እግዚአብሔር ፈቅዶ ዛሬ አንድ ሆነናል እህቴ ሆይ ስሚ ማን ይለያየናል ሥጋሽ ከሥጋዬ አጥንትሽ ከአጥንቴ ተዋሕዶአልና ሆነሻል ሕይወቴ/2/ በእመብርሃን ምልጃ በጌታ ቸርነት በቃልህ ከታመንኩ በዚህ ቅዱስ እለት የአጥንትህ ክፋይ አካልህ ነኝና ጌታዬ ልበልህ ክብሬ አንተ ነህና/2/ አንቺም ተጠበቂ ከዲያብሎስ ሴራ ሰውነትሽ ዘወትር በጐ ምግባር ይሥራ ቅድስና ወደሽ ከኃጢአት ራቂ የሃይማኖትሸን ክር ማእተብሸን አጥብቂ/2/ ከቃልህ አልወጣም ጌታዬ ሆይ ስማኝ እስከመጨረሻው ፍጹም ታዛዥህ ነኝ በቤተክርስቲያን ጥላ ስር በመሆን በቃሉ እመራለሁ አንብቤ ወንጌልን/2/ እግዚአብሔር ሆይ ስማን ቃልኪዳናችንን ጋብቻችንን ባርክ ቀድስ ጐጆአችንን ከዲያብሎስ ሴራ ጠብቀህ እኛን እስከመጨረሻው በቃልህ አጽናን/2/