ወንድና ሴት አድርጐ እንደፈጠራቸው ኋላም ለኑሮአቸው ጋብቻን ሰጣቸው አንዴ ከተጋቡ አንድ ሥጋ ናቸው ከእንግዲህ ወደፊት ይጸናል ፍቅራቸው ደስ ይበለን ሙሽሪት ሙሽራው/2/ አንድ አካል ሆነዋል አምላክ አጣምሮአቸው በምንም ምክንያት ማንም አይለያቸው በጣም ይወዳታል ባል ክብርት ሚስቱን ስለ እርስዋ አሳልፎ ይሰጣል ነፍሱን አዝ --- ለአብርሃም ለሣራ እንደሰጠ ትዳር ለእናንተም ይለግስ የዘለዓለም ፍቅር ኣንቺም እንደሣራ አንተም እንደ አብርሃም ተፋቅራችሁ ኑሩ እስከ ዘለዓለም አዝ --- ለዚህ ላበቃችሁ ለቸሩ አምላካችን ምስጋና ይድረሰው ዛሬ ከሁላችን በሉ ደኅና ግቡ ወደ አዲስ ጐጆአችሁ አምላክ በጥበቡ ፍቅርን ያላብሳችሁ አዝ ---