አጅቡት በእልልታ ሲመጣ ሙሽራው ፍጹም የሚያስደስት የሠርጉ እለት ነው ዘመዶቹ ሁሉ ተቀበሉት ውጡ የሙሽራው መምጫ አሁን ነው ሰዓቱ እልል /2/ እንዘምር በእልልታ ይህን ላደረገ ለሠራዊት ጌታ ሁሉንም በጊዜው ይፈጽማልና ይኸው አበቃቸው ለዚህ መልካም ዜና ሙሽሪት ተደሰች ዝምታው ምንድነው የዳግም ልደትሽ የሠርግሽ እለት ነው አዳም ጐንሽ ቆሞ ሔዋን ሆይ ሲልሽ መንፈሳዊ ሐሴት ይሙላ በልብሽ አዝ --- እህት ወንድሞቿ እናትና አባቷ ተነሡ ዘምሩ ለልጃችሁ ደስታ መሄዷ ነውና ወደ ቤቷ ዛሬ ወደ አዲስ ጐጆዋ ሽኙአት በዝማሬ አዝ --- ቤተሰቦችሽን ሁሉንም ትተሽ መሄድሽ ነውና ወደ መኖሪያሽ ከአማኑኤል ጋራ ባልሽን ይዘሽ ተነሽ ሙሽራዬ ደርሰዋል ሰዓትሽ ከድንግልም ጋራ ሚስትህን ይዘህ ተነሥ ወንድሜ ሆይ ደርስዋል ሰዓትህ አዝ ---