ሙሽራዬ/3/ አበባዬ ከጐንህ የምትሆን እህት አገኘህ የኛማ ሙሸራ እንኳን ደስ አለህ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ለዚህ ካበቃችሁ ቤታችሁ ይመረቅ በፍቅር ያጽናችሁ አዝ --- ወንድም አግተሻል የሚያስብልሽ የእኛማ ሙሽራ እንኳን ደስ አለሽ እግዚአብሔር ይመስገን እኛም ደስ ብሎናል በቤተክርስቲያን ሠርጋችሁ ውብ ሆኖአል አዝ --- እንደነፍስህ አርገህ እንድትወዳት አደራ ሰጠንህ በጌታችን ፊት እንድታስቢለት አንቺም ለአካልሽ አደራ ትላለች ወንጌል እናትሽ አዝ --- በሥጋው ወደሙ ሕይወት አግኝታችሁ ፍሬአችሁም ይብዛ ይባረክ ጓዳችሁ አምላክ ያለበት ነው ይሄ ጋብቻችሁ እስከ መጨረሻው ኑሩ ደስ ብሎአችሁ አዝ ---