በሠርጋችን እለት እንድትባርከን ጌታ ጠርተንሃል በእምነት ሆነን ከእናትህ ጋራ ከእመቤታችን ከመላእክትህ ጋር ና በሠርጋችን ከሐዋርያት ጋር ና በሠርጋችን ከወዳጆችህ ጋር ና በሠርጋችን በገሊላ መንደር እንደተገኘህ ና በእኛ ድንኳንም ጌታ ሰንጠራህ የጥሪ ወረቀት ልከናል እንዳትቀር አንተነህ ክብራችን የቤታችን ፍቅር ነይ ከልጅሽ ጋራ እመቤታችን እንድታሟይልን የጎደለውን ንገሪው ለልጅሽ ባዶው እንዲሞላ በረከት የእርሱ ነው ቤታችንን ይሙላ አዝ --- በጐደለው ሁሉ እየጨመርሸልን ቤታችንን ሁሉ ሙይው እናታችን ለአገልጋዬቹም ድንግል ንግሪአቸው ጠርተን እንዳናፍር ጋኖቹን ይሙላቸው አዝ ---