ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ/2/ ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ በቤተክርስቲያን ጥላ ተከልለው ተክሊል አድርገዋል ሙሽሪት ሙሽራው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ስለተሰጣቸው ሙሽሪት ሙሽራው አበራ ገፃቸው ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ/2/ ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ የተራራቀ አካል አንድ ሆነ በተክሊል እግዚአብሔር ይመስገን እልል/2/ እንበል አጥንትሽ ከአጥንቴ ሥጋሽ ከሥጋዬ አዳም የሰበከው ይኸው ዛሬ ታዬ ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ/2/ ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ የተክሊሊ ብርሃኗ በእኛ መሀል በርቶ ረቂቅ አንድነት ታየ በእርስዋ ጐልቶ ይህን ድንቅ ነገር ለማየት ያበቃን ምሥጢሩን የሚገልጽ እግዚአብሔር ይመስገን ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ/2/ ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ ነጭ መጐናጸፊያ በአንድ ተጐናጽፈው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አረፈ በጥላው ሙሽሪት ሙሽራው ለፍቅር ተሸነፉ ለቁርባን መቁረቢያ ነጭ ልብስ አሰፉ ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ/2/ ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ