ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ/2/ በእግዚአብሔር በሕያው ቃሉ ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ /2/ አዝ --- ወንድና ሴት አድርጐ እንደፈጠራቸው በኋላም በቃሉ አንድ አደረጋቸው እናትና አባቱን የአዳም ልጅ ይተዋል ከሚስቱ ጋር በሰላም በአንድ ይተባበራል አዝ --- ሁለቱም አንድ ሥጋ ሆነው ይኖራሉ ብሎ አስተምሮናል ጌታችን በቃሉ አንድ ሥጋ ናቸው አይደሉም ሁለት የባልና የሚስት ሕይወት ወደፊት አዝ --- እንግዲህ እግዚአብሔር ካጣመራችሁ በሆነው ባልሆነው ሰው አይለያችሁ ለወገኖቻችሁ ምሣሌ ሆናችሁ በክርስትና ፍቅር አምላክ ያኑራችሁ አዝ --- ምንጣፋችሁ ብሩህ መኝታችሁ ንጹህ ስለሆነላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ዓለም እንዲደነቅ ሰይጣን እንዲያፍር በሐዘን በደስታ ይኑራችሁ ፍቅር አዝ ---