መጽዓ መርዓዊ ፍሥሐ ለኩሉ/2/ በሰላም ጻኡ ተቀበሉ/2/ አንድ ያደረገውን ጌታችን በቃሉ/2/ ሊለየው አየችልም የሰው ልጅ በኃይሉ/2/ ሙሽሪት ሙሽራው የሃይማኖት ፍሬ/2/ በቅዱስ ጋብቻ አንድ ሆኑ ዛሬ /2/ እህት ወንድሞቿ ክርስቲያኖች ሁሉ/2/ ሙሽሪት ሙሽራን ሁላችሁ ምሰሉ በሥጋ ወደሙ ደግም በተክሊሉ/2/ የወንጌልን ትእዛዝ በመፈጸማቸው/2/ የብርሃንን ተክሊሊ ደፍተው አየናቸው/2/ በመንፈሳዊ ፍቅር በመተባበር/2/ እንግዲህ ጀምሩ መልካሙን ትዳር/2/