የምሥራች ደስ ይበላችሁ/2/ አሸብርቆ ዋለ ሙሽሮች ሠርጋችሁ/2/ ሕይወታችሁ ሰላማዊ ፍጹም ፍቅር/2/ እንደ ጽጌረዳ እንደአደይ ፈክቶ የሚኖር አማኑኤል ያድርገው መልካም ትሥሥር አዝ --- መተሳሰብ መከባበር ይሁን ግብራችሁ/2/ ሠርጐ እንዳይገባ ዲያብሎስ በትዳራችሁ በጾም ጸሎት ይታጠር ሙሽሮች ጐጆአችሁ አዝ --- ዓይኖቻችሁ የጐረቤት አይመልከቱ/2/ ለወሬ ለሐሜት ጆሮአችሁ አይከፈቱ በችግር በደስታ በጾም ጸሎት በርቱ አዝ --- እግሮቻችሁ ይገስግሱ ወደእውነት/2/ አማናዊ ማእድ ክርስቶስ ወዳለበት በልባችሁ አኑሩት ታላቁን አባት አዝ --- ድንግል ማርያም ቅድስት እናት ለምኚላቸው/2/ የሚፈልጉትን በሙሉ አንቺ አስጪያቸው በሰማይ በምድርም ምልጃሽ አይራቃቸው