ሙሽሮች እንኳን ደስ አላችሁ/2/ ለዚህ ቀን ይኸው ደረሳችሁ በአምላክ ፊት እጅግ ከበራችሁ/2/ በእግዚአብሔር ቸርነት በመልካም ፈቃዱ በቅዱስ ቁርባኑ ዛሬ ተዋሐዱ/2/ በሥርዓተ ተክሊል በሥጋ ወደሙ በመድኃኔዓለም ፊት ጋብቻን ፈጸሙ/2/ አዝ --- በቤተክርስቲያን በፈጣሪያቸው ፊት ሁለቱም አንድ ሆኑ በዚህች ቅድስት እለት/2/ አንድ የሚያደርጋቸው ተነቦ ወንጌሉ በካህኑ መስቀል በረከት ታደሉ/2/ አዝ --- በወንጌል ትእዛዝ በሐዋርያት ቃል በእመብርሃን ፊት ጋብቻቸው ሰምሮአል/2/ በአምላክ ሥጋና ደም ሁለቱም ታተሙ የኅብረት ቃልኪዳን በአንድ ላይ አሰሙ/2/ አዝ --- ጸንቶ የሚያዘልቃቸው የማይለያያቸው ክቡር ቃል ስላለ በመካከላቸው/2/ እስከመጨረሻው አንድ አካል ሆነዋል የአማኑኤል ሥጋ አስተሳስሮአቸዋል/2/ አዝ ---