በክብር ዙፋኑ መርጦ ያስቀመጠሽ ለእኛ ለኃጢአተኞች ተስፋችን አንቺው ነሽ በፍጹም ንጽሕና ቤተመቅደስ ያደግሽ የአማኑኤል የጌታዬ የፈጣሪ እናት በምን እንመስልሽ/2/ ቃና ዘገሊላ ሠርግ ደግሰው አንቺን ከነልጅሽ በክብር ጠርተው ሰዎች ተረብሸው በጣም ተደናግጠው ወይኑ በማለቁ በፍርሃት ተውጠው አዝ --- ወይኑ በመሃል ላይ ማለቁን ሰምተሽ ድንጋጤአቸውን እመበቴ አይተሽ ወደ ልጅሸ ሄደሽ ብትጠይቂላቸው ጋኑን ውኃ ሙሉት ብሎ አዘዛቸው አዝ --- ውኃውን ወደወይን አጣፍጦ ቀይሮ የዶኪማስንም እፍረቱን ሰውሮ እድምተኞች ሁሉ እስከሚደነቁ አምላክ ከእነእርሱ ጋር መሆኑን አወቁ አዝ ---