ኑ ተመልከቱልኝ የአማኑኤልን ሥራ/2/ ኑ ተመልከቱልኝ የእመቤቴን ሥራ ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ/2/ ሐናና ኢያቄም በጸሎት ሲተጉ በፈጣሪያቸው መልካሙን ቢያደርጉ በቅዱስ ጋብቻ ጸንተው ቢራመዱ የአምላክን እናት ድንግልን ወለዱ/2/ ኑ ተመልከቱልኝ የአማኑኤልን ሥራ /፪/ ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ /፪/ ቀን ከሌት ሲጸልይ ዘካርያስ ካህን ኤልሣቤጥም ተግታ ፈጣሪን ብትለምን በእግዚአብሔር ጥበብ በስተእርጅናቸው ቅዱስ ዩሐንስን አክብሮ ሠጣቸው/2/ ኑ ተመልከቱልኝ የአማኑኤልን ሥራ /፪/ ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ /፪/ ጸጋ ዘአብና ቅድስት እግዚእ ኀረያ ለመልካም ጋብቻ ሆነዋል አርዓያ ተክለሃይማኖትን ጻድቁን ያፈሩት ቀን ከሌት ተግተው ነው በጾምና ጸሎት/2/ ኑ ተመልከቱልኝ የአማኑኤልን ሥራ /፪/ ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ /፪/