ሥላሴ ይባርኳችሁ /2/ በሥጋ ወደሙ ዛሬ የከበራችሁ/2/ ሥላሴ ይባርኳችሁ/2/ እመአምላክ ትከተልህ/4/ ፈተና እንዳይገጥምህ ድንግል ትከተልህ እመአምላክ ትከተልህ ሚካኤል በኑሮአችሁ/2/ አርምሞ ማስተዋል ትእግስቱን ይስጣችሁ ሚካኤል በኑሮአችሁ ገብርኤል ከላይ ወርዶ/4/ እርሱ ይራዳችሁ በክንፎቹ ጋርዶ ገብርኤል ከላይ ወርዶ ኡራኤል በምልጃው/4/ የእውቀተን ጥበብ ይስጥህ/ሽ/ በጽዋው ኡራኤል በምልጃው ጊዮርጊስ አይለያችሁ/4/ በፈተና ጊዜ ጽናት ያሳያችሁ ጊዮርጊስ አይለያችሁ አዝ ---