ለእጸ መስቀሉ

ለዕፀ መስቀሉ እናቅርብ ምስጋና /2/
ክርስቶስ በደሙ ቀድሶልና /2/
ጎልጎ ሲኖር አፈር ተንተርሶ /2/
ይኸው ተገኘልን በዕሌኒ ልቅሶ /2/
አጋንንት አይቀርቡም ከሩቅ ይሸሻሉ /2/
እኛ ስንባረክ በዕፀ መስቀሉ /2/
አዝ . . .
ክርስቶስ በደሙ የቀደሰው መስቀል /2/
ድል መንሻ ሆነልን የሰይጣንን ኃይል /2/
በመስቀል ተሰቅሎ ደሙ ባይሆን ቤዛ /2/
ወድቆ ይቀር ነበር አዳም እንደዋዛ /2/
አዝ . . .
ብርሃን ነው ለዓለም የጌ መስቀል /2/
የድሆች መጽናኛ የደካሞች ኃይል /2/
አይሁድ ይክዱል የጌን መስቀል /2/
ለምናምን ድነት የሚሆነን ኃይል /2/
አዝ . . .
አምነው ለተጠጉ ለተከተሉት /2/
መስቀል ፈውስ ነው ይሆናል ድነት /2/
የዲያብሎስን ኃይል የምንመክትበት /2/
መስቀል ነው ቤዛችን ዓለም የዳነበት /2/
አዝ . . .

Rating

5 - of 0
4 - of 0
3 - of 0
2 - of 0
1 - of 0
Avg. Rating

0