ንጽህት ድንግል ቡርክት የአምላክ እናት እመቤት ልጆችሽ ሙሽሮች ሁለቱም አንድ ሆኑ ተዋሀዱ ተጣመሩ በቅዱስ ቁርባኑ/፪/ ፍጹም መንፈሳዊ ልዩ ፍቅር አንቺ ያለሽበት መልካም ትዳር መሠረቱ ዛሬ ልጆችሽ ቅድስት ሆይ ባርኪያቸው ተገኝተሽ አዝ --- ድንግል ጐጆአቸውን ቀድሰሽ እውነተኛ ፍቅር መሥርተሽ በመካከላቸው ተገኝተሽ ሁሉን አሰጪያቸው አማልደሽ አዝ --- ሙሽሮቹም አምነው በምልጃሽ እናታችን ባርኪን ነይ ሲሉሽ ፈጥነሽ ድረሺና በሠርጋቸው ነይ ተመላለሽ መሀላቸው አዝ --- አንቺን ለሚወዱሽ ለሚያምኑሽ የሕይወት አጣፋጭ ቅመም ነሽ ሙሽሮቹም ዛሬ ይጠሩሻል የጐጆዋችን ፋና ነይ ይሉሻል አዝ --- ቃና ዘገሊላ ተገኝተሽ መልካሙን ጋብቻ የባረክሽ ዛሬም ከልጅሽ ጋር በሠርጋቸው ነይ ተመላለሽ መሃላቸው አዝ ---