እልል እልል ደስ ይበለን/2/ አጅበን መጣን ሙሽሮቹን /2/ እልል ብላችሁ ተቀበሉን /2/ እናንተ ሙሽሮች እንኳን ደስ አላችሁ/2/ የአብርሃም የሣራ ይሁን ጋብቻችሁ/2/ መልካም መተሣሳብ ክርስቶስ ይስጣችሁ/2/ ሣራና አብርሃም ሁሉም የሚያውቋቸው/2/ ሁለቱም ቅዱሳን ናቸው/2/ ፍቅራቸውን አይቶ አምላክ ባረካቸው/2/ ለእናት ለአባት ታዛዥ ግሩም ልጅ ሠጣቸው/2/ ለጌታ መሥዋእት እኔ ልቅረብ ያለው/2/ ይስሐቅን ለአብርሃም የሠጠው/2/ በመልካም ጋብቻ በጥሩ ትዳር ነው/2/ ቅዱስ አባታችን ፈጣሪያችን ሆይ ጌታችን አምላካችን ሆይ በአብርሃም ጎጆ እንደገባህበት 2 በሙሽሮቹም ቤት በረከት ሙላበት በቃናዋ መንደር የጠራኽ ሠርገኛ/2/ አምላክ ተገኘልህ ሆነህ እድላኛ /2/ በቃናዋ መንደር የጠራሽ ሠርገኛ/2 ድንግል ጎበኘችሽ ሆነሽ እድለኛ ማርያም ጎበኘችሽ ሆነሽ እድለኛ