ይትባረክ እንደአብርሃም/2/ እኸ ዘለዓለም/4/ይትባረክ እንደአብርሃም/2/ ሙሽሪት ሙሽራው እንደአብርሃም እንኳን ደስ አላችሁ እንደአብርሃም ተከበረ ዛሬ እንደአብርሃም ቅዱስ ጋብቻችሁ እንደአብርሃም አዝ --- በተክሊለ በቁርባን እንደአብርሃም ስለተጋባችሁ እንደአብርሃም እጅጉን ደስ አለው እንደአብርሃም ቅዱስ አባታችሁ እንደአብርሃም አዝ --- በሥርዓተ ተክሊል እንደአብርሃም ከተጣመራችሁ እንደአብርሃም ደስታ ሰላም ይሙላ እንደአብርሃም ይመር ትዳራችሁ እንደአብርሃም አዝ --- እልል በሉላቸው እንደአብርሃም ዛሬነው ሠርጋቸው እንደአብርሃም የተመረጡበት እንደአብርሃም መልካም ጋብቻቸው እንደአብርሃም አዝ --- አንቺም እንደሣራ እንደአብርሃም እርሱም እንደአብርሃም እንደአብርሃም ተፈቅራችሁ ኑሩ እንደአብርሃም እስከ ዘላዓለም እንደአብርሃም አዝ --- በሉ ደህና ግቡ እንደአብርሃም ወደአዲስ ጐጆአችሁ እንደአብርሃም አምላክ በጥበቡ እንደአብርሃም ፍቅርን ያላብሣችሁ እንደአብርሃም አዝ ---