የሀብከ ዮም የሀብከ መድኃኔዓለም እድሜ ማቱሳላ ወአብርሃም/2/ ይስጣችሁ ዛሬ ይስጣችሁ መድኃኔዓለም እድሜ የማቱሳላን የአብርሃም በቅዱስ ጋብቻ ሙሽሮች ተወስናችሁ ክርስቶስ ተገኝቷል በመሃከላችሁ የድንጋዮቹን ጋን ወይኑን/2/ሊሞላበት/2/ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቷል ከዚህ ቤት አዝ --- ደስታውን አይቶ አምላክ ፍጹም ተደስቷል ሊባርካችሁ እጆቹን ዘርግቷል/2/ በሕይወታችሁም ፍቅር/2/ቅመም ሆኖ/2/ ትኅትናን ይስጣችሁ እግዚአብሔር በቶሎ/2/ አዝ --- ሠርጋችሁ እንዲሆን ደስታ ፍቅር የሞላበት በሕይወታችሁ ውስጥ ክርስቶስ ይግባባት በሕይወታችሁ ውስጥ አምላክ ይኑርበት አዝ --- የበረከት ፍሬ ጸጋው እንዲበዛላችሁ/2/ ዛሬ ተደሰቱ አምላክን ይዛችሁ/2/ እራስን በመግዛት እውቀት/2/ተሞልታችሁ/2/ ዛሬ ተደሰቱ አምላክን ይዛችሁ/2/ አዝ --- በሥጋ ወደሙ እግዚአብሔር ስለመረጣችሁ/2/ የመንፈስ ቅዱስም ሕፃናቶች ናችሁ/2/