እንደ አብርሃም እንደሣራ/2/ ሥላሴ ይኑሩ ከእናንተ ጋራ/2/ ቤታችሁ ይባረክ በረከት ይሙላ ፈቅደው ይስጧችሁ ሰላምና ተድላ ቤቱም የሥላሴ ይሁንላችሁ ዘወትር ይኑሩ መሃከላችሁ ጌታዬ በይው ውድሽ ነውና እህቴ በላት ሥጋህ ናትና ጽድቅ የተሞላ ፍሬ ይስጣችሁ አብርሃም ሣራን ሁኑ ጸንታችሁ ቤታችሁ ይከፈት ለእንግዳ ሰው ከፍላችሁ ስጡ ለተራባው መልካሙን ፍሮ አፍሩ ተግታችሁ ስመ ሥላሴን እያሠባችሁ