ተፈሥሒ ቤተክርስቲያን ተፈሥሒ ቤተ ሥላሴ ያሳደግሻቸው ልጆችሽ አብርሃም ሣራን ሲሆኑልሽ ያሳደግሻቸው ሙሽሮችሽ አብርሃም ሣራን ሲሆኑልሽ አዝ --- ትምህርትሽ ገብቶአቸው የወንጌሉ ቃል በኑሮ ሊያበሩ ይኸው ወጥተዋል በክርስቶስ ትምህርት በቃሉ ተመርተው ለዓለም መሠከሩ ተራራ ላይ ቆመው ተፈሥሒ አዝ --- ከእንቅቡ በታች አይደለም መብራቱ በራ እንጂ ለሁሉ ከእነበረከቱ ጢስ የሌለው ሻማ ደምቀው የከበሩ ልጆችሽ ሙሽሮች እንደጧፍ አበሩ፡፡ ተፈሰሒ አዝ --- ሰላም ላንቺ ይሁን ደስ ይበልሽ በጣም የዘራሽው ማሳ ፍሬውን ሲሸከም ካባ ደረብሽለት ለወንዱ ሙሽራ አክሊል ደፋሸለት ከምርቃት ጋራ ተፈሰሒ አዝ --- ቃልሽ ይለውጣል ግሩም ነው ኃያል አመንዝራዎቹን ድንግል ያደርጋል ተገለጠ ክብርሽ በሙሽሮች ዛሬ መከር ሆኖልሻል ባፈራሽው ፍሬ ተፈሥሒ አዝ --- ሰላም ላንቺ ይሁን ደስ ይበልሸ በጣም የዘራሽው ማሳ ፍሬውን ሲሸከም ካባ ደረብሽለት ለወንዱ ሙሽራ አክሊል ደፋሸለት ከምርቃት ጋር ተፈሥሒ አዝ ---