ንሴብሖ ለሥላሴ/2/ ክበር ተመስገን አምላከ ሙሴ/2/ የእኛ አማላጅ እናታችን/2/ ነይ ነይ ወደኛ እመቤታችን/2/ ፈጥነሽ ተገኚ በመሃላችን ና ወደኛ ሚካኤል/2/ መልአከ ምክሩ ለልኡል ከእግራችን ይውደቅ ሳጥናኤል ና ወደኛ ገብርኤል/2/ ከእሳቱ አውጣን ከነበልባል በክንፍህ ጥላ እንከለል ና ወደኛ ኡራኤል/2/ እንደ ቅዱስ እዝራ ሱቱኤል ጥበብን ስጠን ማስተዋል ና ወደኛ በፈረስ/2/ የልደው ፀሐይ ጊዮርጊስ ገድልህን ሰምተን እንፈወስ/2/ ና ወደኛ ተክለሃይማኖት/2/ ይጠብቀን ያንተ ጸሎት ጸንተን እንድንቆም በሃይማኖት/2/