የቤታችን ራስ ልጅሽ ነው አማላጅነትሽ የሚያድነን ነው/2 እመብርሃን/2/ሰላም አንቺ እኮ ነሽ ለቤታችን/2/ ምን አለንና እኛ በጓዳችን የጎደለ ነው ይኸው ማድጋችን ነይ ከልጅሽ ጋር እንድትሞይልን ድንግል እመቤታችን/2/ ያለን ውኃ ነው ከባዶ ጋን ጋራ የጓሮውም ወይን ብዙም አላፈራ የደሃ ጎጆአችን እንዲባረክልን ድንግል አሳስቢልን/2/ በሠራኘታ ምድር ታምራት ያደረገ በኤልያስ አድሮ ሕዝቡን የባረከ ዛሬም እርሱ ነው የቤቱ ሰላም አምላክ መድኃኔዓለም/2/ ጭንቀትን አይተሽ የልብን ሐዘን ታሳስቢያለሽ እንዲጎበኘን እኛም አንቺን ጠርተን ከእፍረት ድነናል ድንግል ክብር ይገባሻል/2/