ባለውለታዬ /፪/ ከአመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ በሩን ቢዘጋብኝ ስምዖን ጨክኖ ዝቅ አድርጎ ቢያየኝ ከአይሁድ ጋር ሆኖ እንድቀርብ ወደ እርሱ አዘዘ ጌታዬ እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባዬ /፪/ ባለውለታዬ /፪/ ከአመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ሥራዬ እንድወርድ ከዛፉ አዘዘ ጌታዬ ማዕረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ /፪/ ባለውለታዬ /፪/ ከአመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ ድንጋይ የጨበጡ ፈራጆች ከበውኝ ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አቆሙኝ ፈረደችባቸው ኃጢአትም በእነርሱ በሰላም ሂጂ አለኝ ምሮኛል ንጉሡ /፪/ ባለውለታዬ /፪/ ከአመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ የማምነውን አምላክ አውቀዋለሁ እኔ በሠራልኝ ሥራ በዕድሜ ዘመኔ ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ ልለየው አልችልም እስከ መጨረሻ /፪/