እልል በይ/4/ ቤተክርስቲያን ሆይ እልል ባይ እልል በይ ቅድስት ቤተክርስቲያን እልል በይ እጅግ ደስ ይበልሽ እልል በይ ልጆችሽ ለተክሊል እልል በይ ስለደረሱልሽ እልል በይ በስርሽ ተምረው እልል በይ በቃልሽ ታንጸው እልል በይ ለዚህ ክብር በቁ እልል በይ አበሩ ደመቁ እልል በይ መልካሙን ቃልሽን እልል በይ ሕይወት የሆነውን እልል በይ አንድ ሰው ለአንድ ነው እልል በይ ብለሽ ያዘዝሽውን እልል በይ እነዚህ ሙሽሮች እልል በይ በቤትሽ የኖሩ እልል በይ የሃይማኖት ፍሬዎች እልል በይ ከክፋ ጠብቀሽ እልል በይ ሠላምን ስጫቸው እልል በይ በትዳራቸው እልል በይ ከህግ እንዳይወጡ እልል በይ በዓለም ተስበው እልል በይ ቤተክርስቲያን ሆይ እልል በይ እንግዲህ ባርኪያቸው