ሙሸራው ከሙሽሪት ጋር በአደባባይ ደምቀው ታይተዋል እልል በሉ ሚዜዎቹ /ሚዜዎቿ/ የደስታ ተካፋዩቹ/ተካፋዩቿ/ እስቲ ዘምሩለት ለሙሽራው በአንድነት ሆናችሁ ወደ አዲሱ ቤት ለሙሽራው መግባቱን አይታችሁ እስቲ ዘምሩላት ለሙሽሪት በአንድነት ሆናችሁ ረዳት አገኘች የእኛ ሙሽራ ጥሩ ወንድምን አዝ --- ሥነምግባር ላለው ለሙሸራው የቀና ሃይማኖት ደስታው ደስታችን ነው የሙሸራው ክብሩም ክብራችን ነው ሥነምግባር ላላት ለሙሽሪት የቀና ሃይማኖት አጅቧት በደስታ ሙሽሪትን በሆታ በእልልታ አዝ --- ስትበቁ ለክብር ለሙሽሮቹ ለመልካም ትዳር ጎጆ ስትቀልሱ ለሙሽሮቹ በእግዚአብሔር ፈቃድ አብነት ለመሆን የእኛ ሙሽሮች ለጓደኞቻችሁ ወልዳችሁ ለመክበድ የእኛ ሙሽሮች እግዚአብሔር ይርዳችሁ