በኃይለ መስቀሉ /4/ ድል ሆነው ወደቁ አጋንንት በሙሉ ዘምሩ ሁላችሁ ለኃይለ መስቀሉ ድል መንሻ ነውና ላመነበት ሁሉ አዝ . . . ሁላችሁ በአንድነት ዘምሩ በእልል ለዕፀ መስቀሉ ለሕይወት መከ አዝ . . . እልል እልል በሉ በያላችሁበት በኃይለ መስቀሉ ጠላት ለጠፋበት አዝ . . . እኛ እንዳንጠቃ በርጉም ጠላችን መስቀሉን እንያዝ ክርስቲያን ሁላችን አዝ . . . እንሰግድለለን የጸጋ ስግደት በእርሱ ላይ ስላለ ኃይለ መለኮት አዝ . . .