በጌቴ ሰማኔ በአትክልቱ ቦታ /2/ ለእኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ/2/ አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት /2/ በእኛ ላይ ደረሰ የዘለዓለም ሞት/2/ መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ/2 ይገርፉት ነበረ ሁሉም በየተራ (2) ተጠማሁ/3/ ሲላቸው/2/ ኦምጣጤ አመጡለት በሃሞት ቀላቅለው/2/ ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ/2/ እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ/2/ በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው /2/ እንዲህ ሲል ጸለየ አባት ሆይ ማራቸው/2/ በረቂቅ ሥልጣኑ ሁሉን የፈጠረ (2) በሰዎች ተገርፎ ሞተ ተቀበረ/2/