የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ /2/ ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ/2/ የሐስት ምስክር አቁመው ከሰሱት /2/ በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት/2/ ጲላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ/2/ ከሮማዊው መንግሥት እንዲኖር ተፋቅሮ/2/ ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ /2/ እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ /2/ በብርሃን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ /2/ በችንካር ላይ ቆሙ ምንም ሳይሰለቹ /2/ የብርሃን አክሊልን ለሰማእት ያደለ/2/ የሾክ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ /2/