መስክሪ ቀራንዮ መስክሪ ጎልጎታ ›› ›› ›› ሊቶስጥራ የተቀበለውን የአምላክን መከራ/2/ ሊሰቅሉት ሲወስዱት መስቀል አሸክመው ስምኦን ቀሬናዊ ከመንገድ አገኘው(2) ከድካሙ ብዛት ሳይሰሉት እንዳይሞት ለቀሬናዊ ሰው ስሞኦን መስቀል አሸክሙት/2/ የአምላክን ትእግሥት በማየት ተደንቆ ጲላጦስ ጠየቀው እንዲፈታው አውቆ /2/ ጌታም መለሰለት ከላይ ካልተሰጠ በእኔ ላይ ልትፈርድ አንዳች ኃይል የለህ/2/ ስቀለው እያሉ ባንድ ላይ ሲጮሁ ጲላጦስ ጨነቀው የሚያደርገው ጠፋው/2/ ከደሙ ንጽሕ ነኝ በማለት ታጠበ የጌታን ንግግር ቃሉንም አሰበ/2/ መከራ መስቀልህ ሲነገር ይጨንቃል ነፍስም ትርዳለች ሥጋንም ይዳከማል/2/ ድካምህን ሁሉ ከንቱ እንዳላደርገው በንስሓ እንባ ኃጢአቴን እጠበው /