አዘነች /2/ እናቱም ጨነቃት እያየችው ልጇን በመስቀል ላይ ሰቅለውት እዩት ተመልከቱት የአምላክን ሥራ በመሰቀል ላይ ሆኖ ለዓለም ሲያበራ አይሁድ ወንበዴዎች ይዘው አሰቃዩት የሾህ አክሊል ሠርተው በላዩ ደፉበት የድንግልን ሐዘን እጽዋት አይተው ያለቅሱ ጀመረ ከመሬት ተደፍተው መች እነሱ ብቻ ፀሐይም ጨለመች የጌታዬን እርቃን እኔ አላይም አለች የሰማይ ከዋክብት የአምላክን ሞት አይተው ወየው/2/ አሉ ከመሬት ተደፍተው በይበልጥ ጨረቃ እርር ክስል አለች ይህንን ስትሰማ መልኳን አጠቆረች ምድርም አዝና ነበር በጣም ተቸግራ ሲገርፉት እያየች ጀርባወን በወይራ ወየው መጨከኑ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ጲላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ ማርና ወተትን የሚመግብ ጌታ አጥቶ ተቸገረ የውኃ ጠብታ ያን ሁሉ በትእግሥት ችሎ አሳለፈና ይመግበን ጀመር ሰማያዊ መና