ሞተሃልና ስለእኔ ምንም ሳይኖርብህ ጥፋት ተከሰህ ተወቅሰህ በጲላጦስ ፊት ኢየሱስ አማለከ ምሕረት ስብሐት ለከ/2/ የአንተ መንገላታት ሁልጊዜ ያሳዝነኛል ሲወራ በመስቀል ላይ ሆነህ ያየኸው መከራ ኢየሱስ የህይወት እጀራ ስብሐት ለከ.2/ ከልኡል ቦታ ዝቅ ብለህ ፈጣሪ ፍጡራን አምላክ በሰው ፊት ተዋርደህ ስለሰው የሞትክ በመስቀል ላይ ተጠማሁ እያልክ ስብሐት ለከ/2 መሐሪ ጌታ ሆይ አሁንም እንደ ቸርነትህ ብዛት የእኛን በደል ሁሉ ሳትመለከት አድነን ከዳግመኛ ሞት ስብሐት ለከ/2/