ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ በመስቀል ሆነህ ›› ›› ድምፅህን በማሰማት ›› ›› ነፍስህን ሠጥተህ ›› ›› ክዋክብት ከሰማይ በሙሉ እረገፉ ጨረቀና ፀሐይ ደም አጎረፉ ብርሃናት ጨለሙ ከሠው ተለያዩ ሥጋ በመስቀል ላይ ተጋልጦ ስላዩ ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ አሰምቶ ጮኸ ተጠማው እያለ ማርና ወተትን ለሚመግበው ሀሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው አካሉ ሲውጋ ውኃ ደም ፈሰሰ በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ የእስራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ ለእነርሱ አሰብክ እንጂ ለአንተስ አላሰብክ እናቱ ስታለቅስ በመስቀል ስር ሆና ዮሐንስን ሰጠ ጠብቆ እንዲያጽናና መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ