ኪርያላይሶን



ኪራያላይሶን (3)
በሰማይ በምድር ሥልጣኑ ያለህ ኪያላይሶን
በፍርድ አደባባይ አንተን አቆሙህ
እኛን አድን ብለህ መራቅ ተፋብህ
በአክሊል እሾህ ላይ በመቃ መቱህ
የተንኮልን ነገር አንዳች ቢያጡብህ
ይህስ ይሳደባል ብለው ከሰሱህ
እሳተ መለኮት ዓለምን የፈጠርክ
ሥጋ በመልበስህ በሰይፍ ተመታህ
በእኛ አመጽ ግርፋት የተገረፍክል ኪርያላይሶን
በሸንጎ እንዳንቀርብ የተሰቀልክልን
ኤሎሄ (2) የሲቃ ድምጽ
ዛሬም ይሰማናል ይህ ጥሪ ቃልህ
ስቃይህን አስታውስን እናነባለን ኪያላይሶን
የምሕረት እጆችህ እንዲዳብሱን
ስለእኛ መከራ ስለተቀበልህ
አሁንም ደግፈን እንዳንጠፋብህ
በእጆችህ ቀድሰህ አንዳልሰጠሃቸው
እስቲ በእሳት እጅህ ተከላከላቸው
አንተ በባሕርይህ ሁሉን ቻይ ሆነህ
በመስቀል ቸንክረው ቀራንዮ አዋሉህ

Rating

5 - of 0
4 - of 0
3 - of 0
2 - of 0
1 - of 0
Avg. Rating

0