ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን ሰቀሉህ ወይ የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ /2/ የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት/2/ ንጹሕ ክርስቶስ ሆነ ወንጀለኛ ብለህኛ ስለእኛ መሰቀል አሸክመው አስረው ገፈፉህ እያዳፉህ/2/ እጅና እግርህን በብረት ተመታ የዓለም ጌታ የሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/ ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ/2/ በመሰቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው/2/ ይቅር ባይ ግልጽ በደላችንን ሁሉ ሳታይ አንተ ቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ /2/