ለእኛ ብሎ ተንገላታ የሁላቸን ጌታ አዳም ቅጠል በልቶ ባመጣው በሽታ/2/ አምላክ ዋለ ቀራንዩ ለብሶ ከለሜዳ አዳም ሕግ አፍርሶ በጎተተው እዳ/2/ ለመስቀሉ ተሰለፈ እየተገረፈ በእጽ ሊፈውሰው በእጽ ላይ አረፈ/2/ ምንም በደል ሳይኖርበት የዓለም መድኃኒት ፍዳን ተቀበለ ለሰው ልጆች ድኅነት/2/ በመሬት ላይ ተንገላታ ሩኅሩኅ ጌታ አዳም ቅጠል በልቶ ባመጣው በሽታ/2/