በትእግሥቱ ብዛት ባይገለጥ ኃይሉ ስቀለው ስቀለው አይሁድ ተባባሉ/2/ የኃያላን አምላክ አልፋና ኦሜጋ እንድኛ ታመመ በለበሰው ሥጋ ኅብስት አበርክቶ የሚመግብ ጌታ ታሰሮ ተገረፈ እንደክፉ ሽፍታ እጅና እሮቹ ታሰረው ብታይ ድንግል አለቀሰች እለች ዋይ ዋይ የሚንቀጠቀጡለት መላእእክት በፈቱ እንደምን በችንካር ተወጋ ደረቱ የንጹሐን አምላክ ወንጀለኛ ተብሎ ዋለ ቀረንዮ እርቃኑን ተሰቅሎ በደል ሳይኖርበት ተሰቀለልን ሞታችንን ሞቶ ሕይወትን ሰጠን