አምን ለማዳን የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው ጌታችን ተሰቅሎ ቢያዩት መላእክት በዝማሬ ፋንታ አለቀሱለት ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤል ገረመው አምላኩ እርቃኑን ተሰቅሎ ስላየው/2/ ነፍሱን ለወዳጁ የሚሰጥ ቢገኝም ለጠላት የሚሞት በጭራሽ አይኖርም ጠላቶቹ ስንሆን ለኛ ሞተው ክርስቶስ ልዮ ነው ወደርም የለው/2/ ውራን ቢያበራ የሞተን ቢያስነሣ በመመስገን ፈንገታ ሆነበት አበሳ ሰማያዊው ዳኛ ሊፈረድበት ተኮስ ቀረበ በጲላጦስ ፊት /2/ በጸሎተ ሐሙስ እለተ እራት የሆነው 2/ አርብ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ፍቀር አስገድዶት ለኛ የሞተው መልካሙ እርኛችን መድሃኒዓለም ነው/2/