ምደረ ቀረንዮ ምደረ ጎልጎታ መድኃኒት ክርስቶስ በአንቺ ተንገላታ/2/ መስክሪ አንቺ ምድር ግኡዚቷ ሥፍራ መድኃኒት ክርስቶስ ያየብሽን መከራ/2/ ደሙ እንደውኃ ሲፈስ መስቀሉ2/ በቀራንዮ ቦታ መከራውን ሲያይ/2/ ፀሐይ ከለከለች ደማቅ ብርሃኗን /2/ ለመሸፈን ብላ የአምላክን እርቃን/2/ በመስቀል ተሰቅሎ ፍቅሩን ገለጸው /2/ በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ እያለ /2/ የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ /2/ እጆቹን እግሮቹን በችንካር ተመተው/2/ ቸሩ መድኃኔዓም እባክህ ማረን/2// ደካሞች ነንና እንዳንቀር ጠፍተን/2/ በቆረሰከው ስጋ ባፈሰሰከው ደም/2/ አቤቱ ተራዳ እስከ ዘላለም/2/