አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ በከሀዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ/2/ ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ ጽድቅን ስለሠራህ በወንጀል ከሰሱህ ለአደም ቤዛ ልትሆን ብዙ ተንገላታህ አዝ --- ቅዱሳን እጆችህ የፊጥኝ ታስረው እደበግ ጎተቱህ ልትምራቸው የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ አዝ --- በዚያ አደባባይ በጲላጦስ ዘንድ አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ ከሐና ቀያፋ ከካህናቱ ደጅ ከእነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአወጅ ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ ሳዶርና አላዶር ጸናትና አዴራ ተፈልገው መጡ ለችንካር መከራ አምስቱ ችክካሮች ቅንዋት መስቀል አይሁዶች አመጡ ገላህን ለማቁሰል ሊየያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ ግፈኞቹ አይሁድ በአንተ ላይ ቀለዱ ምራቅ ተፉብህ አንተኑ ሊጎዱ ለእኛ ወገኖች ሀጢያት ላደከመን የመስቀልህ ጥላ ማረፊያ ይሁነን