በመንግሥትህ አስበኝ/2/ በበደሌ ብዛት /2/ አይተህ አትጣለኝ/2/ ሳስበው በደሌ ብዙ ነው/2/ በጨለማ ነፍሴን በላት ውድማ/2/ ሆዴ ባባ አፈሳለሁ እንባ/2/ እርቃኔን ቀረሁኝ ተገፈፈ ልብሴ መድረሻው ጠፋብኝ ተጨነቀች ነፍሴ የብርሃን ጸዳሌ ከዓይኔ ተገፈፈ ከፊትህ ለመቆም ጉልበቴ ታጠፈ አልቻልኩም ደግፈኝ እንድቆም/2/ ለገነት የበቃ ያቀማኛ ሽፍታ እኔንም ደግፈኝ አውጣኝ የዚያን ለታ/2/