አባታችን ሆይ የሁላችን ጌታ /2/ ቅዱስ መንፈስን ስጠን በተርታ /2/ ወደአንተ መልስ የሰውን ልቡና/2/ ባላወቀው መንገድ እርሱ ሄዷልና/2/ እዝነ ልቡናችንን ወደአንተ አዘንብለን/2/ ይቅርታን ልንጠይቅ ከፊትህ የቆምነው/2/ መሐሪ መሆንህን ስለምናውቅ ነው /2/ አይተህ እንዳላየ ታልፈዋለህ ሁሉንም/2/ መዓቱም ምሕረቱም ሁሉም የአንተ ሲሆን /2/ ሥልጣንህ ረቂቅ ነው አይመረመርም/2/ ዘመንና ወራት ሊሺሩት አይችሉም/2/ የፍቅር ባለቤት ቸሩ አምላካችን /2/ እድሜ ለንስሓ ስጠን ለሁላችን/2/ እንማልድሃለን በልቅሶ በሐዘን/2/ የይቀርታ ብዛት ከእኛ ጋር እንዲሆን/2/ የሰማይ መላእከት የምድር ሰራዊት /2 ያመሰግኑሃል በቀንና ሌሊት /2/