ወንበዴ ነበርኩኝ ሀገር ያስለቸው በመስቀል ላይ ሆኖ ታሪኬን ለወጠው አስበኝ ስላልኩት በኋላ ስትመጣ ገነትን ለማየት የመጀመሪያው ሰው ሆነኩኝ ባለእጣ አዳም ሕግ አፍርሶ ባመጣው በሽታ/2/ አቤት ፍቅሩ የእግዚእሔር/2/ ግሩም ፍቅሩ ›› ›› ኃያል ፍቅሩ ›› ›› ግሩም ፍቅሩ ›› ›› አስበኝ ስላልኩት አሰበኝ ጌታዬ ወንበዴ ነበርኩኝ ስርቆት ነው ሙያዬ በመስቀል ላይ ሆኖ ሕዝቡን ያስብ ነበር እኔስ አላየሁም /2/ እንዲህ ያለ ፍቅር አልታይም ብዬ ኃጢአትን ስሠራ ተመለስ ይለኛል ስሜን እየጠራ እንዳልሞትበት ነው በኃጢአት ታስሬ ፍቀሩን አልዘልቀውም/2/ እንደዚህ ዘርዝሬ መከራ ሲከበኝ መጥቶ ያጽናናኛል በሐዘኔ ጊዜ እግዚአብሔርም ያዝናል ዓይኑ ከእኔ አይርቅም ጥበቃው አይጠፋም ስሙን እጠራለሁ/2/ በጌታዬ አላፍርም