በኢየሩሳሌም በበጎች በር በቤተ ሳይዳ እኖር ነበር ማን ያድነኛል እያልኩኝ አልጋህን ይዘህ ሂድ አለኝ ‹‹ ‹‹ እምነትህ አዳንህ አለኝ ‹‹ ‹‹ አምላኬ መጥቶ ፈወሰኝ በአልጋ ላይ ከዋልኩ ስንብቻለሁ ሰውነቴ አልቆ መንምኛለሁ ውኃውን ሳያማታ ቅዳሜ ቀደመው የዳኑ እኔ ቆሜ አይዞህ የሚለኝ የሚያጽናናበኝ ደገፊም የለኝ ብቸኛ ነኝ ሠላሳ ስምንት ዓመት እያሉ ተሳለቁብኝ መፃጉእ እያሉ እዘንልኝና አድነኝ ሙሉ ጤነኛ አድርገኝ ልትድን ትወዳለህ ሲለኝ እውነትም እውነት አልመሰለለኝ አዎ እወዳለሁ ስለው ጌታ ፈወሰኝ አምላክ የእኔ አለኝታ ስማኝ አምላኬ እጮሃለሁ ኃጢአቱ በዝቶ አለቅሳለሁ በመብል ጠፍቶ ልጅነቱ ባሪያህ አድረገኝ ውድ አባቴ እንደእኔ ታማሚ የሆናችሁ አምናችሁ ጌታ ያድናችሁ እነደእኔ ድውይ የሆናችሁ የጌታ እናት ታመልዳችሁ