የዳዊት ሐዘኑ የጴጥሮስ ንስሓ/2/ እኛን ያነጻናል እንደ ንጹሕ ውኃ/2/ ይቅር ባይ ነህና የሰውን በደል የእኔን አበሳዬን አሁን ይቅር በል የዳዊት ሐዘን የጴጥሮስ ለቅሶ/2/ የተቀበለ አምላክ ተበድሎ ክሶ የዛሬም ይቅር በል የሕዝቡን አበሳ/2/ አንተ የከፈልክልን የእኛ ሁሉ አበሳ በደለኛው እኔ የአንተን ሕግ ጥሼ /2/ ንጹሀ ስጋዬን በጭቃ ለውሼ / በንስሓ ውሃ አጥቤና ስድሼ/2/ አሁን ይቅር በለኝ መጣሁ ተመልሼ