አቤቱ አቤት ኃጢአቴ ብዛቱ/2/ መስፊሪያም የለውም እርስ ካልተወኝ በቸርነቱ ከእኔ ኃጢአት ይልቅ ይበዛል ምሕረትህ አደራ እንድትምረኝ ጌታ በቸርነትህ/2/ እስከ አንገቴ ደርሶ የኃጢአቴ ብዛት ሊውጠኝ ነውና አውጣኝ የእኔ አባት/2/ ለእግሬ መቆሚያ ከሌለው ባሕር ድረስልኝ ጌታዬ ወድቄ እንዳልቀር/2/ ወደአንተ ስጣራ በጩኸት ደክሜ ተስፋ ሊያስቆርጠኝ የኃጢአት ሸክሜ/2/ ወደ ኃላ ልቤ እንዳይመልስኝ መልካም እረኛዬ አንተ ጠብቀኝ/2/ የሠራሁት ሁሉ ከአንተ አይሰወርም ይቅር ትለኛለህ አልጠራጠርም/2/ መመለሴን እንጂ መሞቴን አትወድም በዚህ እጽናናለሁ ከፍቅርህ አልርቅም/2/ አንተን ስበድልህ ይቅር እንዳልከኝ የሚበድሉኝን ይቅር በልልኝ /2/ ይቅርታ ለማድረግ እኔን ቢከብደኝ አንተ አይቸግርህም ይቅርታ ስጠኝ /2/