አደባበይ ቆሜ ስምህን ከመስበክ መጀመሪያ ልቤ ከፊትህ ይንበርከክ ከአገልግሎት በፊት አንተን ልወቅህ መሥዋዕት ከማቅረብ ልታዘዝልህ/፪/ አሐዱ አብ ብዬ ስምህን ብቀድስ ለድሆች ብሰጥ ቤትህ ብገሰግስ በመላእክት ልሳን ብዘምር በእልልታ ምን እጠቅማሃለሁ ካልፈራሁ ጌታ/፪/ ተራራ እስካፈልስ እምነት ቢኖረኝ ሥራ ከሌለበት ምንም አይጠቀመኝም ልቤን ስትመረምር ከሆንኩኝ ቀላል ክርስቲያን መባሉ ምን ይጠቅመኛል/፪/ ጨው አልጫ ቢሆን በምን ይጣፍጣል ከውጭ ተጥሎ በእግር ይረገጣል አንተን ለሚከተል እንዳልሆን እንቅፋት አምልኮቴ ይሁን በፍቅር በፍርሃት/፪/ የዕውቀት ሰው መሆን አልጠቀመኝ እኔስ መስቀልህ ነው ፍቅርህ ያሸነፈኝ ከእምነቴ የተነሳ መታዘዝ የሆነኝ ስምህን መፍራት ነው በእምነት የሚያኖረኝ/2/