በከሃሊነቱ በአምላክነቱ /2/ ይቅር ይለናል ይታደገናል/2/ በቸርነቱ ምን ይከፈለዋል ምን ይሆን ዋጋው ለፈጠረን ጌታ ለይቅር ባዩ የድኅነትን መንገድ ንስሓን የሠራ እንዳንጠፋበት ነው ዳግም በመከራ ይቅር ይለናል ይታደገናል/2/ በቸርነቱ የሰው ልጅ ከኃጢአት እስኪመለሰ ድረስ አይቸኩልም እርሱ መዓትን ለማድረስ ትእግሥቱ ሰፊ ነው ሥራው እረቂቅ ቸርነት ገንዘቡ ቢሰጠው አልያቅ ይቅር ይለናል ይታደገናል/2/ በቸርነቱ