እስራኤል ሰለቸው የሰማዩ መና/2/ ዓለም አምሮት ሄደ ጸጋውን ተወና/2/ የእግዚአብሔር ስጦታ ኅብስቱ ስልችቶት/2/ ዓለም አምሮት ሄደ ከተወው ባርነት/2/ የፈርኦን ጅራፍ አልታየው አለ የእህል አምሮቱን ውርደቱን ከለለ/2/ ግብፅ ልሄድ ብሎ አመጸ በእግዚአብሔር መድርሱ አልገባውም ከከነዓን ሀገር/2/ የኪዳኑ ታቦት የሙሴ ገጽታ ዓለም ስላማረው አደረገው ተርታ /2/ የአምላክን ካህነት የአሮን ሥርዓት በዓለም ለወጠው ትልቁን አምኃ/2/ የኅብረቱን ጉዞ በፍቅር የሄደው የማኅሌት ደስታ እስራኤል ታከተው/2/ የእግዚአብሔርን ድንኳን ደመና ያጀባት የኪዳኑን አርማ በበረሃ ተዋት/2/ ዛሬም ይህ ትውልድ እስራኤልን ሆኗል ቤክርስቲያኑን አምላኩን እረስቷል/2/ ግብጽና ባቢሎን አጓጉተው ወስደውት ወርቁን ከእጁ ጣለ መዳብ አስጎምጅቶት/2/