አዝናለሁ አለቅሳለሁ ስለ በደሌ ሁልጊዜ አለቅሳለሁ አዝናለሁ አለቅሳለሁ ስለጥፋቴ ሁለጊዜ አለቅሳለሁ ነገር ግን መሐሪ ነህና እንደምታድነኝ አምናለሁ/2/ ሥጋዬ ለራሱ እያታለለኝ/2/ ሁለን በመፈለግ ወሰደና ለጥፋት ሰጠኝ ከመሬት ተገኝታ እመሬት ልትገባ/2/ ከንቱ አስቀረችኝ ያሳሳች ሥጋ ሰገብጋባ /2/ ትቻት ልመጣ ነው አፈር ሥጋዬን ›› ›› ›› መሬት ሥጋዬን እንድትቀበላት አምላኬ ሆይ አደራ ነፍሴን/2/