ሞቼ ስለማልቀር ትንሣኤ ስላለኝ በተስፋ ቤታችን ስለምንገኛኝ ወዳጅ ዘመዶቼ አታልቅሱ በቃኝ/2/ አቀናለሁና ገና አዲስ ኑሮ አምላክን አስቡት ይብቃችሁ እሮሮ/2/ ይልቅ ጸልዮላት ለነፍሴ እረፍት ዓለም አታላይ ናት ዘላቂ አይደለች ለሥጋ ነው እንጂ ለነፍስ አትመች/2/ ግን ከሥጋ ጋር ስንኖር ትእዛዙን ከጠበቅን ለተዘጋጀው ቤት ወራሾች እኛው ነን/2/ መቼም ከማያልቀው በረከት ያደልከን ዘላለማዊ ሕይወት ለሰጠኽኝ ምስጋናችን ይድረስህ ጸጋህ አይለየን እኛ በድለን ትህዛዝህን ጥሰን አንተ በመስቀል ላይ ደምህ ፈሰሰልን ፍቅርህን ስናስብ እጅግ ይደንቀናል ለዚህ ሁሉ ውለታህ ምን እንከፍላለን